Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባንኩ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ የተሰኘ ዲጂታል የውጪ ሐዋላ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ (EthioDirect) የተሰኘ ዲጂታል የውጪ ሐዋላ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ጥቅም ላይ አውሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ አገልግሎቱን ይፋ ሲያደርጉ እንዳሉት ÷ ወቅቱን ያገናዘበ ዲጂታል የገንዘብ መላኪያ ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ ፕላትፎርሙ ተዘጋጅቷል፡፡

ደንበኞች ‘EthioDirect’ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር እና አፕስቶር በማውረድ ፣ ሞባይል ስልካቸው ላይ በመጫን ከውጪ ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ ገንዘብ መላክ እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በ https://www.ethiodirect.com ድረ ገጽ አገልግሎቱ እንደሚቀርብ ነው የገለጹት፡፡

የባንኩ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜና ቦታ ከክፍያ ነፃ ሐዋላ መላክ የሚችሉበት ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ እንደሆነ ማስረዳታቸውንም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version