የሀገር ውስጥ ዜና

“ከብዙ ፈተናዎች ጋር እየተጋፈጥን ሳለ፣ኢኮኖሚያችን ጽኑ በሆነ መልኩ እየተጠናከረ ነው” – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Alemayehu Geremew

January 30, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብዙ ፈተናዎች ጋር እየተጋፈጥን ሳለ፣ ኢኮኖሚያችን ጽኑ በሆነ መልኩ እየተጠናከረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ይህን ይበልጥ አጠናክረን ለመቀጠል ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በትብብር ምርታማነት ላይ መሥራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት የገበታ ለሀገር አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ውብ ቦታ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያለፉትን ሥድስት ወራት አፈጻጸም በመገምገም ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡