የሀገር ውስጥ ዜና

በሰላም ስምምነቱ አተገባባር ዙሪያ ለወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ እየተሰጠ ነው

By Melaku Gedif

January 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ስምምነቱ አተገባባር ዙሪያ ለወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡

በመድረኩ በፌዴራል መንግስትና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አተገባበር በተመለከተ ነው ማብራሪያ እየተሰጠ የሚገኘው።

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የሰላም ስምምነቱ አተገባበር ያለበትን ደረጃና አጠቃላይ ሂደት አብራርተዋል።

በዚሁ ማብራሪያ የሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተሳትፈዋል።

የወታደራዊ አታሼዎቹ መንግሰት ለሰላም ስምምነቱ መከበር ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ ተግባሮቹ አሳይቷል፤ይህም ትርጉም ያለውና የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በሐብታሙ ተክለስላሴ