አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ ከመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑ ተወስኗል።
ይህን ተከትሎም ተሳፋሪዎች እጥፍ እንዲከፍሉ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የአንበሳ አውቶብስና ሸገር አውቶብስ ደግሞ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ 30 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መወሰኑንም ነው ያስታወቀው።
ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ይሆናል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision