የሀገር ውስጥ ዜና

ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 200 ብር በታች ለገበያ ይቀርባል

By Tamrat Bishaw

January 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ ማንኛውም የሲሚንቶ ምርት ከ1 ሺህ 200 ብር በታች እንደሚሸጥ የአምራቾች ማኅበር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤቶች የሲሚንቶ ስርጭትን ለመቆጣጠር በወጣው መመሪያና የዋጋ ተመን ዙርያ የአምራቾች ማኅበር መግለጫ ሰጥቷል ።

በመግለጫውም ሲሚንቶ በአዲስ ተመን መሸጫ ዋጋ ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል ብሏል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች በተወሰነለት ዋጋ በመሸጫ ሱቆች እንደሚገኝ ማኅበሩ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ከቀጣዩ ሣንት ጀምሮ÷ ዳንጎቴ ሲሚንቶ 1 ሺህ 106 ብር ከ85 ሳንቲም ፣ ደርባ ሲሚንቶ 1 ሺህ 67 ብር ከ33 ሳንቲም፣ ካፒታል ሲሚንቶ 1 ሺህ 52 ብር ከ25 ሳንቲም እና ኩዩ ሲሚንቶ 1 ሺህ 65 ብር ከ25 ሳንቲም መሸጫ ዋጋ በኩንታል እንደተቆረጠላቸው ተገልጿል።

የዋጋ ተመን ላይም ሁሉንም ዓይነት ምርቶች ከ1 ሺህ 200 ብር በታች እንደሚሸጥ ነው ማኅበሩ የገለጸው፡፡

በተያያዘም በክልል እና ዞኖች የመሸጫ ዋጋ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

አሸናፊ ሽብሩና ምስክር ተስፋዬ