የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ኮንፈረንስ ተካሄደ

By Feven Bishaw

January 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ “የሰላም መንገድ በመከተል ልማታችንን እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

ኮንፈረንሱ በዞኑ ወቅታዊ የሠላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ነው የተካሄደው፡፡

በኮንፈረንሱ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን እና ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ የክልል ፣የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሠብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ሠሞኑን ከድባጢ፣ ወምበራ፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ ማንዱራ፣ ዳንጉር ወረዳዎች እና ከግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።