Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ የከንቲባዎች ልዑክ ኬፕ ታውን ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የተለያዩ የአገሪቱ ከተማዎች ከንቲባዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን የአፍሪካ የከንቲባነት አመራር ኢኒሼቲቭ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬፕ ታውን ከተማ ገባ።

ልዑኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ድረስ ሳህሉ፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴ እና የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝን ያካተተ ነው።

ልዑኩ በፈረንጆቹ ከጥር 23 እስከ 26 በሚካሄደው የአፍሪካ የከንቲባነት አመራር ኢኒሼቲቭ ፎረም ላይ ይሳተፋል።

ልዕኩ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊዎች እና በኬፕ ታውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በፎረሙ ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ ወቅት ከተለያዩ የአህጉሪቷ የከተማ ከንቲባዎች ጋር ልምድ የሚለዋወጥና የሚማማር መሆኑን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።

Exit mobile version