ስፓርት

ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጠ

By Feven Bishaw

January 22, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለአትሌት ታምራት ቶላ የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ለ46 አትሌቶቹ የተለያዩ ማዕረጎችን ሰጥቷል፡፡

በዚህም በኦሪገን ማራቶን ሻምፒዮን የነበረው አትሌት ታምራት ቶላ የዋና ሳጅን ማዕረግ የነበረው ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጥቶታል፡፡

በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ታላላቅ አትሌቶችን እያፈራ ያለ መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በሂርፖ ሺቦ