የሀገር ውስጥ ዜና

መስዋዕትነት ለከፈሉ ዓርበኞች ልጆች የሕፃናት መርጃ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

By Alemayehu Geremew

January 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅልውና ዘመቻው ለሀገር መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ዓርበኞች ልጆች ማሳደጊያ የሚውል የሕፃናት መርጃ ማዕከል በጎንደር ከተማ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የመርጃ ማዕከሉ የመሰረት ድጋይ በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ የተቀመጠ ሲሆን ÷ “ባንቺ የሕፃናት መርጃ ማዕከል” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው ባንችአምላክ ይልማ በተባሉ ግለሰብ ሲሆን÷ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለማዕከሉ ግንባታ የሚውል 1 ሺህ 500 ካሬ ሜትር መሬት ማስረከቡን የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡