የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ ከቻይና አፍሪካ ሙያ እና ቴክኒክ ህብረት ጋር በቅንጅት ለመስራት ተስማማ

By Mikias Ayele

January 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይና አፍሪካ ሙያ እና ቴክኒክ ህብረት ጋር በቅንጅት መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል ።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንዲሁም የመምህራን ስልጠና እና የተማሪዎችን ነፃ የትምህርት እድል ለማገዝ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ  ተሻለ በሬቻ ÷ በዘርፉ ውጤታማ ከሆነችው ቻይና ጋር የተደረገው ስምምነት ጥሩ ልምድን ለማግኘት ያግዛል ብለዋል።

በሚቀጥሉት ወራትም ስምምነቱን ወደ ተግባር የሚቀይሩ ፕሮጀክቶች እንደሚነደፉ ነው የተናገሩት፡፡

ቻይና በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ እየሰራች ያለው ስራ ለዘርፋ የምታደርገው ድጋፍ ጠንካራ መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ድጋፋ  ሚኒስቴሩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ለማዘመን ለሚከናወነው ስራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

በቅድስት አባተ