Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ 2 አመራሮችና 6 ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡
 
በቁጥጥር ስር የዋሉትም አመራሮች፡-
 
1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ
 
2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ
 
ፈፃሚዎች ፡-
 
3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)
 
4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
 
5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
 
6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)
 
7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)
 
8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡
 
የተጀመረው ሕግን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የጸረ ሙስና ኮሚቴ ማስታወቁንም የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version