አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኔፓል በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ67 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
72 ሰዎችን አሳፍሮ ከካትማንዱ ወደ ፖክሃራ ይበር የነበረው የየቲ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰው በማዕከላዊ ኔፓል አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በማረፍ ላይ ሳለ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም እስካሁን የ67 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ነው ሬውተርስ የዘገበው፡፡
የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር ፑሽፓ ካማል ዳሃል ካቢኔያቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸው እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም በሥፍራው ተገኝተው የነፍስ አድን ሥራ እያከናወኑ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ከተጓዦቹ መካከል÷ የሕንድ፣ ሩሲያ፣ የደቡብ ኮሪያ እና የአውስትራሊያ ዜጎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!