Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በህክምናው ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ስፔሻሊስት ሃኪሞችና የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በህክምናው ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 77 ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና 139 የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ተመራቂዎች ከብዙ ልፋት ፣ጥረትና ውጣ ውረድ በኋላ ለስኬት በመብቃት ክቡር በሆነው ሙያ ቃለ መሀላ ገብታችሁ ወገኖቻችሁን በፍፁም ቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል በመብቃታችሁ የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መዲናችን አዲስ አበባን በህክምናው ዘርፍ የቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን ለማስቻል የተያዘው ውጥን ስኬታማ እንዲሆን እየተሰራ ያለውን ስራ የሚደግፍ ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

Exit mobile version