አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን “በሠላም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የወጣቶች ሚና” በሚል ርዕስ ከክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ አሻድሊ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ተፈጥሯዊ ሀብቶችን በሚገባው ልክ መጠቀም ሳንችል ቆይተናል፡፡
ከለውጡ በኋላ የክልሉ መንግሥት በተጨባጭ ሀብቱን መቆጣጠርና ከተፅዕኖ ተላቆ መወሰን በመቻሉ በተለይ በማዕድን ዘርፉ መነቃቃት መፈጠሩንና የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የክልሉን ሕዝብ ከድህነት አላቆ የተፋጠነ ልማትና የመሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በዚህም የወጣቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቱ በተለያዩ አመለካከቶች ሳይጠለፍ በሙሉ አቅሙ ልማቱ ላይ መረባረብ ይገባዋል መባሉን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!