ቢዝነስ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚያዝያ 01 እስከ ሚያዝያ 03 የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገለፀ

By Tibebu Kebede

April 04, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚያዝያ 01 እስከ ሚያዝያ 03 2012 ዓ.ም የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገለፀ።

ባንኩ በፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው፥ የባንኩን የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ አቅም ማስፋፊያ ስራውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ከመጪው ሐሙስ ሚያዝያ 01 ቀን እስከ ቅዳሜ ሚያዝያ 03 ቀን 2012 ዓ.ም. ሙሉ ቀን አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።