Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ ሜሪ ጆይ አረጋውያን ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ ሜሪ ጆይ አረጋውያን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የሰው ልጅ ከተባበረ እና ቅን አስተሳሰብ ካለው በዚህ መልኩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችል በማዕከሉ አይተናል ብለዋል፡፡

በሜሪ ጆይ የአረጋውያን ማዕከል በጎነትንና ኢትዮጵያዊ መተባበርን አይተናል  ነው ያሉት አቶ ደስታ።

የሜሪ ጆይ ማዕከል ለኢትዮጵያውያን የመረዳዳት ትምህርት የሚሆን ተቋም ነው፤በጎ ተግባራችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊያን ብላችሁ መነሳታቸው የሚደነቅ ተግባር  ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ሀገር በቀል ተቋም ድጋፍ ልናደርግ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

ሜሪ ጆይ እየሰራ ያለው ስራ መንግስትን የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው÷ የክልሉ መንግስትም ከጎኑ ሆኖ ይደግፈዋል ማለታቸውንም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የሜሪ ጆይ ማዕከል መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ÷ ርዕሰ መስተዳድሩ ማዕከሉ ድረስ መጥተው በመጎብኘታቸውና የክልሉ መንግስት ለሚያደርግላቸው ቀና ትብብር አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.