የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ7 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

By Melaku Gedif

January 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሰባት ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ፡፡

የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ያስረከቡት የሮማንያ አልጄሪያ ቼክ ሪፐብሊክ ጊኒ ዚምባብዌ ጊኒ ቢሳኦ እና እንግሊዝ አምባሳደሮች ናቸው፡፡

አምባሳደሮቹ ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት መንገድ ላይ መምከራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡