አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ42 ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄዱትን ውይይቶች በተመለከተ ከምሁራን ውይይት አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።
ምሁራን በኢትዮጵያ ልማት ውስጥ ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማጠናከር በሀገር አቀፍ ደረጃ በ42 ዩኒቨርሲቲዎች ውይይት መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በዚኅም የተካሄዱትን ውይይቶች በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምሁራን ውይይት አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር መወያታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡