ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ በረራዎቿ በቴክኒክ ብልሽት ሳቢያ ተስተጓጎሉ

By Alemayehu Geremew

January 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቷ ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ብልሽት ሳቢያ የሀገር ውስጥ በረራዎቿ መስተጓጎላቸው ተገለጸ፡፡

የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳደር እንደጠቆመው ÷ አብራሪዎች ላይ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የሚያስጠነቅቀው ሥርዓት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለማስተካከል እየሰራ ነው።

አስተዳደሩ በአሁኑ ሠዓት ዓየር ላይ የሚገኙ በረራዎች ያለምንም ችግር ማረፍ እንደሚችሉ ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሁለት የሀገሪቷ አውሮፕላን ማረፊያዎች የሚነሱ በረራዎች መቀጠላቸው የተገለጸ ሲሆን÷ በርካታ በረራዎች ግን አሁንም ለተወሰኑ ሠዓታት ተቋርጠው ይቆያሉ ተብሏል።

ጉዳዩም ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት እንደደረሰና ምንም ዓይነት የሳይበር ጥቃት ፍንጭ እንዳልተገኘ ተገልጿል፡፡

ተስተጓጉለው የቆዩት የሀገር ውስጥ በረራዎች አሁን መጀመራቸው ተዘግቧል፡፡

የዓየር ትራፊክ ደኅንነቱም ወደ ቀድሞ ሥርዓቱ መመለሱ ተነግሯል፡፡

አሁንም ግን በመቆጣጠሪያ ኮምፒውተሩ ላይ ደረሰ የተባለውን ችግር በትክክል ለመለየት እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡