አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ መጋቢት 1 ቀን ጀምሮ ወደ ቻይና የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር ከኪቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረበት መጠን ከፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ ቀደም ሲል በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ቻይና የጉዞ ገደቦችን መጣሏን ተከትሎ ወደ ቻይና ከተሞች የሚያደርገውን የበረራ መጠን ቀንሶ ቆይቷል።
ሆኖም ቻይና ያስቀመጠቻቸውን የጉዞ ገደቦች ማንሳቷን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድበፈረንጆቹ መጋቢት 1 ቀን ጀምሮ ወደ ቻይና የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር ከኮሮና በፊት ወደ ነበረው የበረራ መጠን ከፍ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡