Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል ተጭኗል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትግራይ ክልል ነዳጅ ማጓጓዝ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካለፈው እሁድ ድረስ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል መጫኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለጸ፡፡

በባለስልጣኑ የነዳጅ አቅርቦት፣ ሎጅስቲክስና ክትትል ዳይሬክተር ፈቃዱ ሹመት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ 25 ቦቴ ናፍጣ እና 3 ቦቴ ቤንዚን ወደ ሽረ፣ መቀሌ፣ አጉላ፣ ውቅሮ፣ ዛላንበሳ እና ኩይሓ ከተሞች ተጭኗል፡፡

እያንዳንዳቸው ከ45 ሺህ እስከ 50 ሺህ ሊትር የመጫን አቅም ያላቸው 28 ቦቴዎች ወደ ትግራይ ክልል መጫኑን አረጋግጠዋል፡፡

በባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በቀለች ኩማ እንደገለጹት÷141 ሺህ 151 ሊትር ቤንዚን እና 1 ሚሊየን 189 ሺህ 923 ሊትር ናፍጣ በድምሩ 1 ሚሊየን 331 ሺህ 074 ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል ተጭኗል፡፡

ነዳጁን ወደ ክልሉ እንዲያደርሱ የጫኑት ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች፥ ኦይል ሊቢያ፣ ኖክ፣ ታፍ፣ ቶታል፣ ዳሎል፣ ሓለፋይ እና የተባበሩት መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ኖክ አንድ ጊዜ ከጎንደር ዲፖ ወደ ሽረ መጫኑን እና ሌሎቹ ግን ከጅቡቲ በቀጥታ መጫናቸው ነው የተገለጸው፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version