የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 171 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

January 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 171 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ተመላሾቹ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ ውስጥም አስሩ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሴቶችእና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 26 ሺህ 695 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡