ስፓርት

ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ

By Mikias Ayele

January 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ፡፡

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ÷ በዓለም ዋንጫው የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በመተካት ነው በዛሬው ዕለት የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት፡፡

የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ፈርናንዶ ጎሜዝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከፌዴሬሽኑ የቀረበላቸውን የአሰልጣኝነት ጥያቄ በደስታ መቀበላቸው ገልጸዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የ49 ዓመቱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በ2024 በሚካሄደው የአውሮፓ ዋንጫ እንዲሁም  በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በሚዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድንን ይመራሉ፡፡