Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር ምሽት 1ሰዓት የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ቡድኑ ከሞሮኮ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ራባት መሐመድ ስድስተኛ እግር ኳስ አካዳሚ ተገኝቷል።

ጨዋታውም ምሽት 1 ሰዓት እንደሚጀመር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለቻን ዝግጅት ሞሮኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከሞሮኮ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version