ቢዝነስ

ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርአት መገልገላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

By Tibebu Kebede

April 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ሥርዓት መገልገላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበ።

ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ባለፉት ሁለት ሳምንታት 6 ሺህ 592 ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክስ ፋይል ሥርዓትን ተጠቅመው ግብራቸውን እንዳሳወቁ ተናግረዋል።

አቶ ላቀ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የግብር ሥርዓት መገልገላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

አሠራሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመከላከል ባሻገር የግብር ከፋዮችን ጊዜ እና ወጪ በመቆጠብ የግብር ሥርዓቱን ለማዘመን ይረዳል ተብሏል።

1 ሺህ 685 ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ሥርዓት ግብር መክፈላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision