Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር ተወያዩ

ANKARA, TURKEY - AUGUST 18: Turkish President Recep Tayyip Erdogan (R) and Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed (L) hold a joint press conference at the Presidential Complex in Ankara, Turkey on August 18, 2021. (Photo by Ali Balikci/Anadolu Agency via Getty Images)

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻንጋር በስልክ ተነጋግረናል ብለዋል።
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እና ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማምተናል ነው ያሉት።
Exit mobile version