አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለምሻምፒዮና የ10ሺህ ሜትር አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን አሸነፈች፡፡
ውድድሩ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ለ40ኛ ጊዜ በሱሉልታ ሲካሄድ የአለም ቻምፒዮኖች፣ የኦሊምፒክ ኮከቦችና ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡
የጃንሜዳን የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በማሸነፏ በዚህ አመት በአውስትራሊያ በሚካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክላ የምትፋለም ይሆናል።
እንዲሁም አትሌት ጌጤ አለማየሁ 2ኛ፣ አትሌት መቅደስ አበበ 3ኛ፣ አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ 4ኛ፣ አትሌት ፎቴን ተስፋዬ 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ የአዋቂ ወንዶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸናፊ ሲሆን÷ አትሌት ታደሰ ወርቁ፣ አትሌት ጌታነህ ሞላ፣ አትሌት ሞገስ ጥኡማይ፣ አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ፣ አትሌት ሀይለማረያም አማረ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል።
በወጣት ሴትቶች 6ኪሎ ሜትር አትሌት ለምለም ንብረት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ አትሌት መልክናት ውዱ፣ አትሌት ትነብ አስረስ እስከ ሶስት ባለው ደረጃ አጠናቀዋል።
በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ደግሞ አትሌት በረከት ዘለቀ፣ አትሌት ቦኬ ድሪባ፣ አትሌት አቤል በቀለ ቀዳሚዎቹን ደረጃዎች ይዘው ጨርሰዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!