አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ በሽረ ዲስትሪክት ተጨማሪ ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በሽረ ዲስትሪክት ስር በሚገኙት÷ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ዕዳጋ አክሱም፣ ሶሎዳ፣ ዓዲ አቡን፣ ዓዲ ማሕለኻ፣ ካሌብ፣ ንግስተ ሳባ እና ሮምሃይ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ባንኩ ታኅሣሥ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሽረ፣ በእንዳስላሴ፣ ምድረ ገነት፣ ዕዳጋ ሽረ፣ ስሑል ሽረ እና ምድረ ሓየሎም ቅርንጫፎቹ ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በቀጣይ ሁኔታዎች እንደተመቻቹ ቀሪ ቅርንጫፎቹን ዳግም ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ባንኩ ዝግጁ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!