የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓድዋ ከተማ የባንክ አገልግሎት ጀመረ

By Feven Bishaw

December 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት በዓድዋ ከተማ ዳግም የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ባንኩ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገዉን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተሞች ዳግም የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውሷል።

ከእነዚህ ከተሞች በተጨማሪ ዛሬ በዓድዋ ከተማ የባንክ አገልግሎት ዳግም መስጠት መጀመሩን ገልጿል፡፡

በቀጣይም በመቀሌና በሌሎች ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎችን ዳግም ለመክፈት ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ መጠቆሙን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡