አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሞ ባንክ በ2014 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባንኩ በዛሬው ዕለት የባለ አክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉዔውን አካሂዷል።
የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ከበደ ÷ ባንኩን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከነባር ባለ አክሲዮኖች በተጨማሪ አዳዲስ ባለ አክሲዮኖችን ለማፍራት ጥረታችንን አጠናከረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ዓለማየሁ ኃይለ ጊዮርጊስ በበኩላቸው ÷ ኦሞ ባንክ ባለፋት ጊዜያት በእያንዳንዱ ቤት ገብቶ የብዙዎችን ሕይወት መለወጥ መቻሉን አንስተው አሁን ያለውን ሐብት 12 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱም 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር ማሰራጨት መቻሉ ተመልክቷል፡፡
ባንኩ ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማሳደግ በደቡብ ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦችና በሲዳማ ክልል ቅርጫፎችን በመክፈት ሂደት ላይ ነው ተብሏል፡፡
በጥላሁን ይልማና ቢቂላ ቱፋ