ቢዝነስ

በመዲናዋ የዳቦ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

April 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የዳቦ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ ተቋማት ላይ ህጋዊ አርምጃ እንደሚወሰድ የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ያለ ምንም ምክንያት የዳቦ ዋጋ የመጨመር እና ግራም የመቀነስ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ለማወቅ አንደተቻለ ነው የገለፀው።