የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ ተገናኝተው ተወያዩ

By Mekoya Hailemariam

December 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኝተው ተወያዩ።

አዛዦቹ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ መክረዋል።

ውይይቱን የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ሌሎች የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች መርተውታል።