የሀገር ውስጥ ዜና

በ3ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው የቂርቆስ ፓርክ ግንባታ ተጀመረ

By Amele Demsew

December 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17 ሚሊየን ብር የሚገነባውና በ3ሺህ ካሬ ሜትር ወለል ላይ ያርፋል የተባለው የቂርቆስ ፓርክ ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ግንባታውን የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ቢቂላ ሁሩሳ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በይፋ አስጀምረውታል፡፡

ቦታው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ከቄራዎች ድርጅት ፊት ለፊት ያለው ሰፊ ቦታ ሲሆን ፥ ግንባታው በደቡብ ግሎባል ባንክ የሚከናወን መሆኑን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፓርኩ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከመዝናኛነቱ ባሻገር ፣ የንባብ ቦታዎች ፣ የህፃናት መጫዎቻዎች፣ የሻይ ቡናና ቶሎ የሚደርሱ ፈጣን የምግብ አገልግሎቶች፣ የህዝብ መፀዳጃና ሌሎች ስራ ዕድሎችን እንደሚፈጥርም ተገልጿል፡፡