Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመከላከያ ሚኒስቴር ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መጻሕፍትን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስቴር ለአብርሆት ቤተመጻሕፍት ከ3 ሺህ 500 በላይ መጻሕፍት ማበርከቱ ተገለጸ።

መጻሕፍቱ አጠቃላይ ግምታቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን ለመማር ማስተማር የሚሆኑ የተለያየ ይዘት ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ ለአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ መጻሕፍቱን አስረክበዋል።

መጻሕፍቱ ከመከላከያ ጤና መምሪያ፣ ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ ከመከላከያ ዩኒቨርሲቲ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ በግል ተነሳሽነት የተበረከቱ መሆናቸውን ተመላክቷል።

ሚኒስትሩ መጽሐፍቱ ትውልድን ለመገንባት ሊጠቅሙ የሚችሉ በርካታ ይዘት ያላቸው ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ በበኩላቸው ለሀገር ለውጥ ቁልፍ መሳሪያ ለሆነው የትምህርት ግብ መሳካት አንባቢ ትውልድ መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል።

Exit mobile version