Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፈረንሳይ ሞሮኮን በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ አለፈች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአል ባይት ስታዲየም አንድ ጨዋታ ተደርጓል፡፡
 
በዚህም ፈረንሳይ አፍሪካዊቷን ሞሮኮ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች።
 
የፈረንሳይን የማሸነፊያ ግቦች ቲዮ ሄርናንዴዝ በ5ኛው እና ኮሎ ሙአኒ በ79ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡
 
ውጤቱን ተከትሎ ፈረንሳይ የፊታችእሑድ ከአርጀንቲና ጋር ለፍጻሜ ጨዋታ የምትፋለም ይሆናል፡፡
 
ትናንት ምሽት በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና ክሮሺያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፏ የሚታወስ ነው፡፡
Exit mobile version