Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሳሊቫን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም÷በጦርነቱ ማቆም አተገባበር፣ በመንግሥት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሥራዎች ላይ መክረዋል፡፡
እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማደስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version