የሀገር ውስጥ ዜና

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ35 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

December 12, 2022

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ35 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

ህብረቱ ድጋፉን ያደረገው የገጠር ልማታዊ የሴፍቲኔት ፕሮግራምን ለማገዝ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ትብብር እንዳለው ጠቁመው፥ በተደረው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ህብረቱ ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በተገኙበት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶይማ ፔትሬስኮ ተፈራርመዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ