Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 150 የውሃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር ለበጋ መስኖ ልማት አገልግሎት የሚውሉ 150 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ድጋፍ አድርጓል።

የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ወጌሾ በሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው ከኢንጂነር አይሻ መሐመድ ተረክበዋል፡፡

ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ ሚኒስቴሩ በቀጣይ የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ይደግፋል፡፡

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍ በክልሉ እየተተገበረ ላለው የልማት ሥራ አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version