Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉትን ጨምሮ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉትን ጨምሮ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

በዚሁ መሠረት ዛሬ በሚካሔድ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የአፍሪካ ብቸኛ ተወካይ ሆና የቀረችው ሞሮኮ ከፖቹጋል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማሉ፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ እንግሊዝ ከፈረንሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡

ትናንት በተካሔዱ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ክሮሺያ ብራዚልን እንዲሁም አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተቀላቅለዋል፡፡

Exit mobile version