የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን አስመልክቶ በሀዋሳ ሲምፖዚየም ተካሄደ

By Shambel Mihret

December 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በሐዋሳ ሲምፖዚየም ተካሂዷል፡፡

በሲምፖዚየሙ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት ተሳትፈዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በሲምፖዚየሙ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ዛሬም ወደፊትም እኛ ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች ነን ብለዋል፡፡

ሀገራችን በዘመናት መካከል በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሟትም ፈተናዎቹ ኢትዮጵያውያን ይበልጥ ጠንካራ አንድነት እንዲኖራቸው አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ከሕዝባችን ጋር ሆነን ዘላቂ ሰላም መገንባት አማራጭ ሳይሆን የህልውናችን ጉዳይ ነው ብለዋል አፈ ጉባዔው አገኘሁ፡፡

በኅብረ ብሔራዊነትና በአንድነት መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡