የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

By Feven Bishaw

December 06, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ ማስጀመሪያ ላይ መልክት ያስተላለፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ እና ራሽያ ያላቸውን ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት አንስተዋል።

ሩሲያ በሳይንስ፣ በትምህርትና ሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መድረኩ ሳይንስ፣ ቴክኒክ፣ ኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች የሚያጠናክሩበት እንደሚሆን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ባለው የአገር በቀል ምጣኔ ሀብት በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች ያሉ አማራጮች ላይ የራሺያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።