Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን የተመለከቱ መረጃዎች።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 723 ሺህ 700

ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151 ሺህ 991

በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች 34 ሺህ

በቻይና 31 አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል

በኒውዮርክ 1 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል

በጣሊያን የሟቾች ቁጥር ቅዳሜና እሁድ ሲቀንስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 97 ሺህ 689 አድጓል

አሜሪካ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መሆኑን ተከትሎ አካላዊ ፈቀቅታን እስከ ፈረንጆቹ ሚያዝያ 30 ቀን 2020 ድረስ አራዝማለች

ኔፓል ዜጎቿ ከቤት እንዳይወጡ ያሳለፈችውን ውሳኔ እስከ ፈረንጆቹ ሚያዝያ 7 ቀን 2020 ድረስ ማራዘሟን ይፋ አድርጋለች

ጃፓን ከአሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም በአጠቃላይ ከአውሮፓ የሚገቡ ተጓዦችን ልታግድ መሆኑ ተነግሯል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version