Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኦቻ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን እያከናወነ ያለውን ሥራ አደነቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) መንግስት በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን እያከናወነ ያለውን ሥራ አደነቀ፡፡

በኦቻ የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የገንዘብና ሀብት አሰባሰቢ ክፍል ዳይሬክተር ሊዛ ዳውተን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ዳሰሳ ሪፖርትን ይፋ ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኦቻ በኢትዮጵያ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በሪፖርታቸው ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ለስደተኞች አስፈላጊውን ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ ችግሮች ለተጎዱ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ጠይቀው÷ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version