የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣልያን ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

December 02, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣልያን ምክርቤት የውጭ እና የአውሮፓ ህብረት ማህበረሰብ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ጂሉዮ ትሪሞንቲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ደሚቱ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ስለምታደርገው  አስተዋፆኦ እና በአፍሪካ ከፍተኛ የስደተኞችን ቁጥር በመቀበል ለቀጠናው ስለምታበረክተው አስተዋፅኦ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጁሊዮ ትሬሞንቲ በበኩላቸው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቻቸው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር አብሮ ለመስራት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡