አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ደቡብ ኮሪያ ፖርቹጋልን ተከትላ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች።
በምድብ 8 ማምሻውን 12 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያ ፖርቹጋልን 2 ለ 1 በማሸነፍ በ4 ነጥብ በግብ ክፍያ ጥሎ ማለፉብን ተቀላቅላለች።
በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ አፍሪካዊቷ የምድቡ ተወካይ ጋና በዑራጋይ 2 ለ 0 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች።
ውጤቱን ተከትሎም ፖርቹጋልና ደቡብ ኮሪያ ጥሎ ማለፉን ሲቀላቀሉ፥ ዑራጋይ እና ጋና ከዓለም ዋንጫው ተሰናብተዋል።