የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ አርማ ወርሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ሊጀምር ነው

By Feven Bishaw

March 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኘው አርማ ወርሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በነገው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ሊጀምር ነው፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ በብቸኝነት ምርመራ ከሚያደርገው ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተጨማሪ አርማ ወርሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ እንደሚጀምር የኢንስቲትዩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደጅይጥኑ ሙላው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ለምርመራው የሚሆኑ የላብራቶሪ ቁሳቁሶች እና የሰው ሃይል መሟላታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ምርመራውም እንደ ሃገር ያለውን የመመርመሪያ ቦታ ለማስፋት ያለመ እንደሆነ ደጅ ይጥኑ ሙላው ተናግረዋል፡፡

 

በፌቨን ቢሻው