የሀገር ውስጥ ዜና

የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች የፊታችን ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የቨርቺዋል ኮንፈረንስ ሊያካሂዱ ነው

By Tibebu Kebede

March 28, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት(ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች የፊታችን ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያተኮረ የቨርቺዋል ኮንፈረንስ ሊያካሂዱ ነው።

ኮንፈረንሱ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭትን በቀጣናው በቅንጅት መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር መሆኑን የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናግረዋል።