አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በሬዲዮና የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው እንዳስታወቀው ትምህርቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤት መዘጋቱን ተከትሎ የሚሰጥ ነው።
በዚህም ሳምንቱን ሙሉ ረፋድ ከ3 እስከ 4 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ9 እስከ 10 ሰዓት ድረስ ትምህርቱ የሚሰጥ ይሆናል ነው ያለው።