Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ካናዳ ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ተሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ካናዳ በክሮሺያ 4 ለ 1 መሸነፏን ተከትሎ ከውድድሩ ሁለተኛዋ ተሰናባች ሀገር ሆናለች።

የካናዳው አልፎንሶ ዴቪስ በዛሬው ጨዋታ ክሮሺያ ላይ በ2ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፈጣኗ ጎል ሆና ተመዝግባለች።

ከዚህ ቀደም የኔዘርላንድሱ ኮዲ ጋክፖ በ6ኛው ደቂቃ የውድድሩን ፈጣን ጎል ኢኳዶር ላይ ማስቆጠሩ ይታወሳል።

ካናዳ በክሮሺያ መሸነፏን ተከትሎ ከኳታር ቀጥሎ ሁለተኛዋ ተሰናባች ሀገር ትሆናለች።

Exit mobile version