Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ ከሚሰሩ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተ ከኢንቨስተሮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይት መድረኩ የክልሉ አርብቶ አደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም ሌሎች የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
በእርሻ ልማት የተሰማሩ ባለሃብቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናግረዋል፡፡
ይህ ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ አወል ያረጋገጡት።
በክልሉ ማህበረሰብና በባለሃብቶች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት የእርሻ ልማቱ እንዳይስተጓጎል መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በተለይ በስንዴ ልማት ሊያጋጥሙ የሚችሉ መሰናክሎችን መንግሥት እንደሚያስተካከል ተናግረው÷ ባለሃብቶችም ጠንክረው እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ከርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version